ምስጋና
ኢሳት የኢትዮጵያ ህዝብ አይን ጆሮ እንዲሁም አንደበት! ኢሳት የሚደገፈው እንደናንተ ባሉ ተመልካቾቹ እና አድማጮቹ ነው!
Washington DC Metro ESAT Support Chapter
ESAT Ethiopian New Year Event 2011 (2018)
የተከበራችሁ የኢሳት የዋሽንግተን ዲሲ ሜትሮ አካባቢ አባላት እና ደጋፊዎች፡ ባለፈው ቅዳሜ (Sep. 15, 2018) የኢሳት የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ክብረበዓል ላይ ለመሳተፍ ጊዜያችሁን እና ገንዘባችሁን መስዋዕት አድርጋችሁ የመጣችሁ ፤ በተለያየ ምክንያት መምጣት ሳትችሉ ትኬቱን ከድረ-ገፃችን ላይ እና ከሌሎች ቦታዎች በመግዛት የተባበራችሁ በሙሉ ዝግጅታችን ያማረ ፤ የደመቀ እና ውጤታማ የሆነ እንዲሆን ላደረጋችሁት አስተዋፅዖ የአዘጋጅ ኮሚቴው እና የኢሳት የዋሽንግተን ዲሲ ስቱዲዮ ከልብ የመነጨ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ ይህ ዝግጅት በርካታ አባላቶቻችን እና ደጋፊዎቻችን ወደ ውድ አገራችን ለተልዕኮ የተጓዙበት ወቅት በመሆኑ ምናልባት ይህ ዝግጅት እንደቀድሞው ዝግጅቶቻችን ውጤታማ ላይሆን ይችላል የሚል ስጋት ነበረን፡፡ ነገር ግን ከጠበቅነው በላይ አዳራሻችን ሞልቶ ታዳሚዎቻችን በንቃት አና በደስታ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ያዋጡበት የተዝናኑት እንዲሁም ከወዳጅ ጉዋደኞቻቸው እና ከአላማ አጋሮቻቸው ጋር በአይነስጋ የተገናኙበት ወቅት ነበረ፡፡ እጅግ ኮርተናል፡፡ የኢሳት ደጋፊዎቸ እና አባላቶች እጅግ በርካታ እና ኢሳት ድረሱልኝ ፤ ደግፉኝ ባላቸው ጊዜ በፍጥነት ሮጠው ከጎኑ የሚቆሙ መሆኑን ያረጋገጥንበት ወቅትም ነበር፡፡
To Support Call: 1-888-772-3278
በዚህ በአዲስ ዓመት የኢሳት ዝግጅት ላይ በኢሳት ዋና ስራ አስኪያጅ (Executive Director) ጋዜጠኛ አቶ አበበ ገላው እና የድርጅቱ መስራች እንዲሁም የስምሪት ክፍል ዋና ሃላፊ (Chief Operating Officer, COO) አቶ ግሩም ይልማ ንግግሮች እና ገለፃዎች በሰፊው እንደተብራራው ኢሳት በኢትዮጵያ ውስጥ አዳዲስ ስቱዲዮዎችን ማደራጀት ፤ ዘጋቢዎችን እንዲሁም የዜና ማዕከሉን አስተዳደር ሰራተኞች እና መዋቅር በመዘርጋት ስራዎች ላይ ተጠምዶ ይገኛል፡፡ በዚህም ምክንያት ኢሳት የኢትዮጵያውያንን ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ፤ የሙያ እና የቁሳቁስ እርዳታ ይሻል፡፡ ኢሳት የተለያያየ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ተሸከርካሪዎችን ይፈልጋል፡፡ ኢሳት ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እንደ ቪዲዮ ካሜራ ፤ ሚክሰርስ የቢሮ ቴክኖሎጂዎችን ሌሎችም የቢሮ እቃዎች እንዲሁም ብዙ ለድርጅቱ የተቀላጠፈ ሙሉ እንቅስቃሴ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ከኢትዮጵያውያን በእርዳታ ይቀበላል፡፡ ስለሆነም በኢትዮጵም ሆነ በተቀረው የዓለም ዙሪያ የምትገኙ ኢትዮጵያውያኖች እነዚህን እርዳታዎች ለኢሳት በመለገስ ኢትዮጵያውያን ላለፈው ስምንት ዓመታት ማግኘት የጀመሩትን አማራጭ መረጃ በተጠናከረ መንገድ ማግኝት እንዲቀጥሉ ታስችሉ ዘንድ የዋሽንግተን እና አካባቢዋ የኢሳት የድጋፍ ኮሚቴ የበኩሉን ጥሪ ያስተላልፋል፡፡

በመጨረሻም የአዲስ አመት ዝግጅታችን የተሳካ እንዲሆን በቀጥታ እርዳታችሁን ያደረጋችሁ የዋሽንግተን ዲሲ እና አባባቢዎ የንግድ ተቋማት ፤ ምግብ እና መጠጥ በማዘጋጀት በማቅረብ በማስተናገድ በአካል ተገኛታችሁ እርዳታ ያደረጋችሁ እህቶቻችን እና ወንድሞቻችን እንዲሁም የኢሳት የዋሽንግተን ዲሲ ስቱዲዮ እና የዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የድጋፍ ኮሚቴ አባላት እና ቤተሰቦች ከፍተኛ ምስጋና ይገባችኋል፡፡ ያለናንተ ተሳትፎ ይህ ዝግጅት ውጤታማ ሊሆን በፍፁም አይችልም ነበር፡፡ የዋሽንግተን ዲሲ የኢሳት የድጋፍ ኮሚቴ
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መስቀል አደባባይ ቅርንጫፍ Addis Ababa Ethiopia
ESAT USA
P.O.Box 11261,
Alexandria, VA 22312

ESAT Editor
editor@ethsat.com
Use this email for
. Ideas and suggestions to improve our programs
. Forwarding reliable news and info
+31687154530

ESAT Radio
radio@ethsat.com
+15713354024
+15713051637 (Listeners comment recording)

ESAT Support Line
+1888 772 ESAT (3728)
helpdesk@ethsat.com
. Reporting malfunctioning and mistakes to be corrected on our website
. Other issues related to technical matters
. Issues related to public relations or ideas to support ESAT

ESAT Sales & Marketing
marketing@ethsat.com
. inquiries on advertising with ESAT TV, radio, website, social media
. ESAT merchandise sales
. Other issues related to Sales and Marketing
. To connect with the ESAT support group in your area.

ESAT Human & Material Resource
hr@ethsat.com
Use this email to
. become a volunteer with ESAT (journalist, video editor etc)
. contribute technical materials to ESAT
. All issues related to human and material resource

ESAT International Support
esat-international@ethsat.com
Use this email for
. If you are interested in forming an ESAT Support groups in your city or country
. To connect with the ESAT support group in your area
. All issues related to ESAT international support network